Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle cover logo

Mission Berlin 19 – ፍቅር በቀዝቃዛው ጦርነት

5m · Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle · 18 Feb 13:44

የቀሩት 40 ደቂቃዎች ናቸው። አናና ፓውል ቀይ ለባሿን ሴት አምልጠው ምዕራብ ጀርመን ይገባሉ። ፓውል ነገሮቹን ግራ የሚያጋባ ያደርጋል። ከአና ፍቅር እንደያዘው ይነግራታል። ዕድል ወይስ እንቅፋት? አና ተልኮዋን ለመወጣት ምስራቅ ጀርመን መግባት አለባት። ግን ምዕራብ ነው ያለችው። ሌላም ችግር አለ። በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ፓውል ከሷ ፍቅር እንደያዘው ይነግራታል። ተልኮዋን እንድታቋርጥ ይፈልጋል። ተጫዋቹ ደግሞ ተመልሳ ወደ 2006 ዓ ም እንድትመለስ ይፈልጋል። በተጨማሪም አዲስ አላማ እንድታዘጋጅ ይፈልጋል። የቀሩት 35 ደቂቃዎች ይበቃቸው ይሆን አላማውን ለማሳካት?

The episode Mission Berlin 19 – ፍቅር በቀዝቃዛው ጦርነት from the podcast Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle has a duration of 5:00. It was first published 18 Feb 13:44. The cover art and the content belong to their respective owners.

More episodes from Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

Mission Berlin 24 – ሰዐቱ ይሮጣል

አና በ 1961 ዓ ም የደበቀችውን የብረት ሳጥን መልሳ ታገኘዋለች። ስለዛገ ግን መክፈት ያቅታታል። ሲሳካላት ደግሞ ያረጀ ቁልፍ ታገኛለች። የሚስጥር ቁልፍ ይሆን? ሰዐቱ ይሮጣል። አና የብረት ሳጥኑን መክፈት አለባት። ተጫዋቹ ግን ሌላ ሰው ባለበት ማህሌቱን እንዳትከፍት ያስጠነቅቃታል። ሳጥኑ ውስጥ አሮጌና የዛገ ቁልፍ ታገኛለች። ቀይ ለባሿን ሴት ለማሸነፍ አሁን ቶሎ ብላ ወደ 2006 ዓ ም መመለስ አለባት። ለዚህ ግን በቂ ጊዜ ይቀራት ይሆን?

Mission Berlin 25 – በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ

ሰዐቱ እየጠበበ ነው። አና ፓውልን መሰናበት አለባት ወደ ህዳር 9 2006 ዓ ም ለመመለስ። ተልኮዋን ለማሳካት 5 ደቂቃዎች ብቻ ናቸው የቀሯት። ይበቋት ይሆን? ተጫዋቹ አና ያለውን ግርግር ተጠቅማ እንድትጠፋ ይመክራታል። አና ግን ፓውልን ሳትሰናበት መጓዝ አትፈልግም። የጨዋታውን ውጤት ስትመዘግብ የዛገው ቁልፍ እንቆቅልሹን ለመፍታት የሚያስፈልጋት አንደኛው ቁልፍ እንደሆነ ትደርስበታለች። ሌላኛው ደግሞ ሙዚቃው ነው። ግን መጥፎውን ነገር እንዳይከሰት ለማድረግ በሰዐቷ ትደርስ ይሆን? ተልኮዋን ለማሳካት 5 ደቂቃዎች ብቻ ናቸው የሚቀሯት።

Mission Berlin 26 – የጊዜ ተሞክሮ

ወደ አሁን ስንመለስ አና ከፓውል ጋር የድሮውን የሚያስታውሰውን ነገር ለመዝጋት ትሞክራለች። ግን የሚስጥር ቁልፉ ይጠፋታል። አና ሙዚቃውን ትከተላለች። ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትላለች። ሀላፊዋ የ አናን እቅድ ግብ ከመግባቱ በፊት ታበላሽ ይሆን? አና ወደ ጥንት ትመለሳለች። ፓውልን የዛገውን ቁልፍ ታሳየዋለች የድሮውን የሚያስታውሰውን ነገር እንዲቀረቅርበት። ግን ለዛ የሚስጥር ቁልፉ ያስፈልጋታል። እሱ ደሞ የላትም። አና የዳህፌግስን ስም በመስጠት ለመዝጋት ተሞክራለች። ባለቀ ሰዐት ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትልና ቁልፉን እንድትሰጣት ትጠይቃለች። አና ቁልፉን ማሽን ውስጥ ትከትና የሚስጥር ቁልፉን ትሰጣለች። ቀይ ለባሿ ሴት የድሮውን የሚያስታውሰውን ነገር እንዳይበላሽ ማድረግ ትችል ይሆን ወይስ እሷም እንደ ማሽኑ ታሪክ ሆና ትቀራለች?

Mission Berlin 23 – እስከ በኋላ

አና በሞተር ሳይክል ወደ በርንአወር መንገድ ትወሰዳለች። የሚወስዳት ሰው ኤምረ ኦጉር ይባላል። መልካም ጊዜ በበርሊን ይመኝላታል። ግን ከቀይ ለባሿ ሴት ለማምለጥና የብረቱን ሳጥን ለማግኘት ይበቃት ይሆን? ተጫዋቹ አና ጊዜ ስለሌላት ወደ በርንአወር መንገድ የሚወስዳት ሰው እንድትፈልግ ይመክራታል። አናን በሞተር ሳይክል አንድ ወጣት ሰውዬ ፤ የበኋላው መርማሪ ኤምረ ኦጉር ይወስዳታል። ከዚያም አና ሀይድሩንና ፓውልን ስታገኝ ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትላለች። ፓውልና የሀይድሩን ባል ሊያባርሯት ይችላሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ አና ማህሌቱን ለማምጣት መንገድ ትጀምራለች። ግን ማህሌቱ ከብዙ አመታት በኋላ አሁንም እዚያው ይሆን ያለው?

Mission Berlin 22 – እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጂ

አና ወደ በርሊን 1989 ዓ ም ፤ በግንቡ መፍረስ የተነሳ ትልቅ ደስታ ወደሚታይበት ከተማ ትመለሳለች። በዚህ ግርግር ተጋፍታ ማህደሩን መውሰድ አለባት። ይሳካላት ይሆን? ልክ አና ወደ 1989 ዓ ም ልትጓዝ ስትል ጥቁር ኮፍያ የሚያደርጉት ብቅ ይላሉ። ቀይ ለባሿ ሴት አናን እንዲፈልጉ ትዕዛዝ ትሰጣለች። በህይወት እንዲያመጧት! አና ግን የድሮውን ነገር በሚያስታውሰውን ነገር በሰዐቷ የበርሊን ግንብ ወደ ፈረሰበት ቀን ትመለሳለች። የብራንድቡርገር በር ጋር ግርግር ውስጥ ቆማለች። ግን ወደ በርንአወር መንገድ መሄድ አለባት። 30 ደቂቃዎች ብቻ ናቸው የቀሯት። ግን ከዚህ ግርግር በሰዐቷ ተከፋፍላ ከነበረችው ከተማ መውጣት ትችል ይሆን?

Every Podcast » Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle » Mission Berlin 19 – ፍቅር በቀዝቃዛው ጦርነት