Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle cover logo
RSS Feed Apple Podcasts Overcast Castro Pocket Casts
Amharic
Non-explicit
dw.com
5:00

We were unable to update this podcast for some time now. As a result, the information shown here might be outdated. If you are the owner of the podcast, you can validate that your RSS feed is available and correct.

It looks like this podcast has ended some time ago. This means that no new episodes have been added some time ago. If you're the host of this podcast, you can check whether your RSS file is reachable for podcast clients.

Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

by DW.COM | Deutsche Welle

Mission Europe ለጀማሪዎች የተዘጋጀ የቋንቋ ትምህርት ሲሆን ፦ Mission Berlin ፦ Misja Kraków እና Mission Paris የሚሰኙትን ልብ ሰቃይ ወንጀል ነክ ታሪኮችን አካቶዋል። ወደ ቋንቋው ዓለም በመዝለቀ የፖላንድኛ፣የ ጀርመንኛ ወይም የፈረንሳይኛ ቋንቋ ይማሩ።

Copyright: 2024 DW.COM, Deutsche Welle

Episodes

Mission Berlin 16 – የድሮ ጓደኛ

5m · Published 18 Feb 13:17
በ 1961 ኛው ዓ ም አናን የታጠቁት ሞተር ሳይክል ነጂዋች ያባርሯታል። በዚህ አስፈሪ ጊዜ አንዲት የማትታወቅ ሴት ትረዳታለች። ግን ለምን ትረዳታለች? አናስ ልታምናት ይገባል? ሞተር ሳይክል ነጂዎቹ አናን ይከታተሏታል። እሷም ወደ ምግብ መሸጫ መደብር እሸሻለች። የሱቁ አለቃ እየዘጋ እንደሆነ ሲነግራት አንዷ ተቀጣሪ አና ጓደኛዬ ነች ትላለች። ገነዘብ ተቀባይዋ አናን ወደ ቤቷ ትወስድና የ ት/ ቤት ጓደኛዋ ነኝ ትላለች። አና ትጠራጠራለች ግን ተጫዋቹ አና ሴትዬዋን ማመን እንዳለባት ይነግራታል። አና የ ገነዘብ ተቀባይዋ ቤት የሴትየዋን ወንድም ፓውል ቪንክለር ትተዋወቃለች።

Mission Berlin 15 – የጊዜ ጉዞ

5m · Published 18 Feb 11:24
አና ከተከፈለችው ምስራቅ በርሊን ወደ ምዕራብ በርሊን መመለስ አለባት። ግን ይህ ብቻ አይደለም። በ 55 ደቂቃዎች ውስጥ RATAVA ምን እንደሆነ ጭምር፤ የበርሊን ግንብ ምስረታ ወይስ ፍርስ? አና 1961 ኛው ዓ ም እንደደረሰች ወደ ካንት መንገድ ለመሄድ ትሞክራለች። ይህ ግን ሊሳካ አይችልም። ምክንያቱም የDDR መንግስት የግንብ ግንባታውን ስለጀመረና አና ደግሞ በምስራቁ በኩል ስላለች። ግን የካንት መንገድ ምዕራብ በርሊን ነው የሚገኘው። ጨዋታውን እንደ አዲስ ካደሱ በኋላ አናና ተጫዋቹ ሁለት ታሪካዊ ክስተቶች ያገኛሉ፦ የ RATAVA አላማ ሊሆን የሚችሉ። የበርሊን ግንብ ምስረታ ወይስ ፍርሰት። ተጫዋቹና አና ይህንን ለማወቅ 55 ደቂቃዎች ብቻ ነው የሚቀራቸው።

Mission Berlin 13 – የእግዚያብሄር እርዳታ

5m · Published 18 Feb 11:16
ቤተ ክርስትያኒትቱ መረጃ ለመሰብሰብ ትክክለኛ ቦታ ሳትሆን አትቀርም። ቄሱ ለአና የሙዚቃው ቅንብር የድሮውን ነገር የሚያስታውስ ቁልፍ እንደሆነ ያብራራላታል።ግን ምን አይነት መሳሪያ ማለቱ ነው? ጨዋታው እንደ አዲስ ከተጀመረ በኋላ አና ከቀይ ለባሿ ሴት ታመልጣለች። ቄሱ ለአና መርማሪ ኦጉር እንደቆሰለና ሆስፒታል እንደተኛ ይነግራታል። ለአናም የሙዚቃውን ቅንብር በድጋሚ ያሰማትና የሙዚቃው ኖት አደራደር D A C H F E G የድሮውን ነገር የሚያስታውሰን ቁልፍ እንደሆነ ያብራራላታል። ይኼ ድል ለተጫዋቹና ለአና የአስር ደቂቃዎች ሽልማት ያስገኛቸዋል። ግን ጊዜው ይበቃቸው ይሆን?

Mission Berlin 12 – የ ቤተ ክርስትያን መዝሙር

5m · Published 18 Feb 11:13
አና 65 ደቂቃዎች ይቀሯታል። የመጫወቻው ቀፎ የቤተ ክርስትያኑ ኦርጋን አካል መሆኑን ትደርስበታለች። ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትልና ከአና ቁልፍ ትጠይቃለች። ግን ምን አይነት ቁልፍ? የቤተ ክርስትያኑ ኦርጋን ከመጫወቻው ቀፎ ጋር አንድ አይነት የሙዚቃ ቅንብር ይጫወታል። አና ቀረብ ብላ የቤተክርስትያን አገልጋዩ ለጎብኝዎች የሚለውን ታዳምጣለች። ኦርጋኑ መታደሱን፤ የበርሊኑ ግንብ ከተሰራ በኋላ ግን ኦርጋኑ አንድ አካል እንደሚጎለው ይናገራል። አና የመጫወቻው ቀፎ የቤተ ክርስትያኑ ኦርጋን አካል መሆኑን ይገባታል። ኦርጋኑ መጫወት ሲጀምር አንድ በር ይከፈትና ቀይ ለባሿ ሴት ፊት ለፊቷ ትቆማለች። አና አንዱን ህይወቷን ታጣለች። የቀራትም 60 ደቂቃዎች ብቻ ነው።

Mission Berlin 11 – ፈጣን ምግብ

5m · Published 18 Feb 10:40
አና ምግብ ከፓውል ጋር እየበላች ስለሚገርመው አረፍተ ነገር ፤ "In der Teilung liegt die Lösung. Folge der Musik!" ታወራለች። እሱም አደጋውን ያውቅና ወደ ቄስ ካቫሊር ጋር ይልካታል። ግን ይኼ ትክክለኛው መንገድ ነው? ፓውል የመጫወቻ ቀፎውን ጠግኗል። ግን የሙዚቃውን ቅንብር እስከ መጨረሻው ለማጫወት አንድ ነገር ይጎለዋል። አና ስለሚያስደንቀው መልዕክት ትነግረዋለች "In der Teilung liegt die Lösung. Folge der Musik!" ፓውል የመጫወቻ ቀፎውን ይሰጣትና ወደ ቄስ ማርኮስ ካቫሊር ጋር ጌትሰማኔ- ቤተ ክርስትያን ይልካታል። ተጫዋቹ ይኼ ቤተ ክርስትያን የምስራቅ ጀርመን (DDR) መንግስት ተቃዋሚዎች መገናኛ ቦታ እንደነበር ለአና ይነግራታል።

Mission Berlin 10 – መውጫ የሌለው መንገድ

5m · Published 18 Feb 10:33
ተጫዋቹ እ ኤ አ ነሐሴ 13 1961 የበርሊኑ ግንብ የተሰራበት ቀን እንደሆነና ህዳር 9 ደግሞ ግንቡ የፈረሰበት ቀን እንደሆነ ይደርስበታል። የአና ተልኮ ከነዚህ ቀናቶች ጋር የተያያዘ ነው። አና ምን ማድረግ ትችላለች? ፓውልና አና ካድቬ ወደሚባል ገበያ አዳራሽ ከቀይ ለባሿ ሴት እየሸሹ ነው። የገበያ አዳራሹ አና የጨዋታዋን ውጤት የምታስቀምጥበት ቦታ ነው። ተጫዋቹ እ ኤ አ ነሐሴ 13 1961 የበርሊኑ ግንብ የተመሰረተበት ቀን እንደሆነና ህዳር 9 ደግሞ ግንቡ የፈረሰበት ቀን እንደሆነ ለአና ያብራራል። አና የተልኮዋ ሙሉ መልስ ከበርሊን መገንጠል ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይገባታል።

Mission Berlin 09 – ያልተሟላ ጥቆማ

5m · Published 18 Feb 10:10
አና ከቲያትር ቤቱ ትጠፋለች። ግን ቀይ ለባሿ ሴት የፓውል ሱቅ እስከምትገባ ድረስ ትከታተላለች። በሀይድሩን እርዳታ አማካኝነት አና ማምለጥ ትችላለች። እንቆቅልሹን ለመፍታት ሙሉ መረጃ የላትም። የተቀረውን ከየት ታገኝ ይሆን? መርማሪ ኦጉር አናን ከጊዜው ሽብር ፈጣሪዎች ፤ RATAVA እንድትጠነቀቅ ይነግራታል። ወደ ሰዐት መሸጫው ስንመለስ፤ ፓውል ቪንክለር የተጠገነውን የመጫወቻ ቀፎ ያሳያታል። የ ፍሪድሪክ ኦጉስት ዳህፌግ "Nostalgie" የሙዚቃ ቅንብር ትጫወታለች። "Unsere Melodie, Anna", ይላል ፓውል። ግን አና ምንም አይገባትም። በድንገት ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትልና ተኩስ ትከፍታለች። ሀይድሩን ድራይ በቦታው ትገኝና ፓውልና አና ማምለጥ እንዲችሉ ታደርጋለች። አና አሁን ሁለት መረጃ ነጥቦች አግኝታለች። እ ኤ አ ነሐሴ 13 1961 እና ህዳር 9። ግን የትኛው አመት ነው?

Mission Berlin 08 – ያልተዘጋ ሂሳብ

5m · Published 18 Feb 10:05
ኦጉር ከቀይ ለባሿ ጋር በተከፈተው የተኩስ ልውውጥ ይቆስላል። ለአናም ስለ RATAVA ታሪካዊ ክስተት ይገልፅለታል። እንደምንም ብሎ እ ኤ አ ህዳር 9 ይላታል። ግን በየትኛው አመት? መርማሪ ኦጉር አና ቲያትር ቤት እንደተደበቀች ይገምትና እንድታመልጥ ይገፋፋታል። ቀይ ለባሿ ሴት አና ላይ ትተኩስና አና አንድ ህይወት ታጣለች። ጨዋታው እንደገና ከተጀመረ በኋላ ኦጉር ለአና ፤ በቡድን ያሉ የጊዜው ሽብር ፈጣሪዎች ታሪክ ሊቀይሩ እንደሚፈልጉ ይነግራታል። ምንም እንኳን መርማሪው በሞት አፋፍ ቢሆንም አናን ወሳኝ የሆነውን ቀን ህዳር 9 ይጠቁማታል። ግን በየትኛው አመት ማለቱ ነው?

Mission Berlin 07 – የማይታወቀው ጠላት

5m · Published 18 Feb 10:00
አና ሞተር ሳይክል ነጂዎቹን ወደ ቫሪቴ ቲያትር ቤት ሄዳ ታመልጣለች። እዛም ሀይድሩንንና መርማሪ ኦጉርን ታገኛለች። እሱም RATAVA እያሳደዷት እንደሆነ ይነግራታል። ግን RATAVA እና ቀይ ለባሿ ሴት ከአና ምንድን ነው የሚፈልጉት? ተጫዋቹ አና ወደ ፓውል ቪንክለር ሱቅ ሄዳ የመጫወቻ ቀፎውን ይዛ እንድትመጣ ያዛታል። ወደእዛ ስትሄድ ሞተር ሳይክል ነጂዎቹን ታመልጣለች። ቲያትር ቤት ሀይድሩን ድራይ ን በድጋሚ ታገኛታለች። መርማሪ ኦጉርም እዛ ብቅ ይልና ሀይድሩን አና የት እንዳለች ይጠይቃል። አና ቲያትር ቤቱ እንደተደበቀች ይጠራጠርና RATAVA እየተከታተሏት ስለሆነ እንድትጠነቀቅ ይላል። ወዲያው ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትላለች። ከአና ምንድን ነው የምትፈልገው?

Mission Berlin 06 – ቀይ ለባሿ ሴት

5m · Published 18 Feb 09:43
አና በ 1961 ጓደኛሞች ነበርን የምትል አንዲት ሴት ታገኛለች። በመጨረሻም አናን አንዲት ቀይ ለባሽ ሴት እንደምትከታተላት ዜና ይደርሳታል። የማይታወቁ ሰዎች አናን በየቦታው ይጠብቋታል። አንዷ ሀይድሩን ድራይ ነች። ከአና ጋር በ1961 ጓደኛ ነበርኩ የምትል። እሷም አናን ለመርዳት ትፈልጋለች። አንዲት ቀይ ለባሿ ሴት አናን እየተከታተለች እንደሆነም ታስጠነቅቃታለች። ለመሆኑ ሀይድሩን ድራይ እንዴት ይሄን ልታቅ ቻለች?

Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle has 25 episodes in total of non- explicit content. Total playtime is 2:05:00. The language of the podcast is Amharic. This podcast has been added on November 27th 2022. It might contain more episodes than the ones shown here. It was last updated on February 15th, 2023 14:35.

More podcasts from DW.COM | Deutsche Welle

Every Podcast » Podcasts » Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle